አውደ ምሕረት


Leave a comment

ኢሳት ይጠየቅልኝ!

ዝርዝር ጥልቀት ያለው ሐተታ ቀርቶ የውጣ ቃልም ብትሆን ስለ ኢሳት አንጻራዊ አመለካከት ማንጸባረቅ፡ ተቋሙ እየተከተለው ያለውን አሰራርና እየሄደበት ያለው ማንንም የማይጠቅም መንገድ እንደ ዜጋ በግልጽ መናገር: ትንፍሽ ማለት በተለይ “ይውደም!” ከተባለ “ይውደም!”- “ይቅደም!” ከተባለም እንዲሁ በተመሳሳይ ድምጽ “እንዴትና? ለምን?” በሌለበት ሁኔታ “ይውደም!” በማለት ድምጹን በማስተጋባት በሚታወቀው ማህበረሰብ አካባቢ ዘንዳ ምን ዓይነት ስም ሊያሰጥ እንደሚችል በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የደርግ ወታደራዊ መንግስት ቀን ጨለማ ሳይል የንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ ሲያደርግና በገዛ ሕዝቡ በአደባባይ በጥይት ሲደበድብ/ሲረሽን አገኘሁበት የሚለው ክስ አንዱ “ጸረ አብዮት ነው!” በማለት ነበር ሲሉ ከሞት ያመለጡ ምስክሮች እንደሚናገሩት ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ መስመሩ ስለ ለቀቀና አቅጣጫው ክፉኛ ስቶ ስለሚገኘው: ታማኝነት የጎደለበት፡ ከምንም በላይ ደግሞ የሞያው ስነ ምግባር በሚጣረስ መልኩ ሆነ ተብሎ እየተደረገ ያለው የኢሳት አሰራር ጭብጥ ላይ የተመረኮዘ ተጨባጭ ሃሳብ ይዤ መመጎቴ ተከትሎ በጸሐፊው የ/ለሚለጠፉ ታቤላዎች አግባብነት የለውም ችግሩም ይቀርፈዋል የሚል እምነት የለኝም።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመልከተ በተለይ ከወቅቱ ጋር በተያያዘ የሃይማኖት መሪዎች የእርስ በርስ የመተረማመሱ ነገር እንዲሁም
በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች በኩል ከመንፈሳዊነት ይልቅ እልከኝነት የተሞለበት ስብእናቸው አይሎ ከመውጣቱ የተነሳ የከሸፈውን እርቀ ሰላም በኢሳት በኩል ያለ አንዳች ተጨባጭና ደረቅ ማስረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ለማድረግ የተሰሩ “ዜናዎችና ሐተታዎች” ብዛቱ ስፍር ቁጥር የለውም። ይህ የምለው ደግሞ እንደ ወንጌል አገልጋይነቴ እውነቱ እውነት ለማለት እንጅ ለመንግስት ጥብቅና ለመቆም ቃጥቶችም አይደለም። ቀደም ሲል በእኔ በኩልም ሆነ በሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና መምህራን አማካኝነት ከዚህ ሁሉ የሃይማኖት መሪዎች ትርምስ ጀርባ ለመልካም ነገር የሚያበቃ አቅም ባይኖረውም ለሁከትና ለረብሻ ግን የሚስተካከለው የሌለው “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት ራሱን የሚጠራ ስመ መንፈሳዊ አጽራረ ጽድቅ ድርጅት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የማፈራረስ ዓላማ አንዱ ስትራቴጂ መሆኑ በተጨባጭ ሲነገር መክረሙን የምንዘናጋው እውነት አይደለም።
ሰሙኑ ከወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ ግልጽ እንዳደረገው ደግሞ ይህ ግብረ እከይ ማህበር (“ማህበረ ቅዱሳን”) አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ሳይቀር ራሱ ጨምሮ በአባልነት እንደሚገኝበት ነበር በይፋ የተነገረው። ታድያ ይህን የመሰለ ሕዝብ ሊሰማውና ሊያውቀው የሚገባው ጥብስ የሆነ ዜና በኢሳት ዘንድ በዝምታ መታለፉ ብቻ ሳይሆን የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ታይቶኝ ነገሩ አግራሞት ስለጣለብኝ ነው ኢሳት ይጠየቅልኝ! የሚል ጽሑፍ ይዤ ብቅ ለማለት የወደድኩ።
 የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ሕዝብን በፈጠራ ወሬ ማደናገር ከሆነ:
 የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ሕዝብን የሚያንጽ ስራ መስራት መሆኑ ቀርቶ እውነት እንዳይገለጥ በመትጋት ለአመጸኛ ጥብቅና መቆም ማለት ከሆነ ኢሳት ይጠየቅልኝ! በማለቴ የሚቆጣ አንባቢ ይኖራል ብዬ አላምንም።
 እንግዲያውስ ኢሳት ይጠየቅልኝ! ተቋሙ እደርስለታለሁ ለሚለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታማኝነቱ የሚገልጠው ሕዝብን ከመናቅ የሚመጣ/ንቀት በሚወልደው የግብር ይውጣ ስራ በመስራት ነው?
 ኢሳት ይጠየቅልኝ! “ማህበረ ቅዱሳን” ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አልፎ በሀገር ደረጃ እያደረሰው ያለ በደልና ግፍ ሕዝብ እንዲያውቀው ያልተፈለገበት ምክንያት ምንድ ነው? ማህበሩ በትውልድ ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት እንደ ልማት የሚቆጠርበት ምክንያቱ ምንድ ነው?
 ኢሳት ይጠየቅልኝ! “የማህበረ ቅዱሳን” አገር አውዳሚ ትውልድ በታኝ መሰሪ ድርጊት በአደባባይ ተራቁቶ ሳለ “ማህበረ ቅዱሳን” እናንተ ጋር ደርሶ በመልካምነት የሚፈረጀበት ምስጢሩ ምንድ ነው?
 ኢሳት ሆይ! ማህበሩ (“ማህበረ ቅዱሳን”) ያልሰራውን ሰራ፡ ያልሆነውን ነው በማለት የሌለ የጽድቅ አክሊልና ካባ እየደራረባችሁ ስለ ማህበሩ ጽድቅ ማውራት ያላሰፋራችሁ የተገለጠ ገበናው ለሕዝብ ከማድረስ መቆጠብን የመረጣችሁበት ምክንያት ምንድ ነው?
 ጎበዝ! እንደው ኢሳት ምን የሚሉት ውል “ከማህበረ ቅዱሳን” ቢፈራረም ነው ይህን ይክል በእውነት ላይ የጨከነው?
 ኢሳት ይጠየቅልኝ! 6ኛው የፓትሪያርክ ምርጫ በተመለከተ የምርጫ ሂደቱ ተቃውሞ ቢገጥመውና ተቃውሞውም “በማህበረ ቅዱሳን” መሪነት ቀርቶ አንዲት ፐርሰንትም ብትሆን “የማህበረ ቅዱሳን” እጅ ኖሮት ቢከናወን ኢሳት ደግሞ ይህችን አግኝቶ ትንሽዋን አግዝፎና አጉልቶ ደህና ዜና ከመስራት ይመልስ ነበር? አጋጣሚውን በመጠቀውም ስለ ማህበረ ቅዱሳን” የሌለውን እየሰጠ ከመናገር ይቆጠብ ይኖር ይሆን? አስችሎት ዝም ይል ነበር ወይ? ጎበዝ ዳኝነትህን ስጥ እንጂ።
 ኢሳት ሆይ! የምለው ከተሰማና ጥያቄዬም ግልጽ ከሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን’ነውሳ አሁን ዝም አላችሁ? ሹመቱ በመንግስት ግፊት ከሆነ የመንግስት ስራ ደግሞ “ማህበረ ቅዱሳን” እየሰራ መሆኑን በይፋ ከተነገረ ምን ነው ዝም ያላችሁ? እያለ ነው። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የሃይማኖት መሪዎች 6ኛ ፓትሪያሪክ ለመሾም ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው በማስመልከት ለሕዝብ በይፋ ባሳወቁበት ሰዓት “ማህበረ ቅዱሳን” የተባለ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎቹ አቃም ከመደገፍ አልፎ በመሪነት መሳተፉን በይፋ ሲገለጽ ሳትሰሙት ቀርቶ ይሆን? ወይስ ሊቀ ጳጳሱ በቴሌቪዥን መስኮት መግለጫውን ሲያነበንቡት በዲሲና በአምስተርዳም ሳተላይት የሚያጨልም በረዶ ይዘንብ ነበር?
 ኢሳት ይጠየቅልኝ! ያለ አንዳች ጭብጥና መረጃ መንግስትን ከመክሰስ ይልቅስ ፈጥቶ የወጣውን እውነት መዘገብ አይቀልም ነበር ወይ? “ማህበረ ቅዱሳን” የህወሐት ተቋሞች/ኢፈርት በማለት ከሚታወቁ መካከል አንዱ ቢሆን ኖሮ አልያም ደግሞ ባያብል ሙላቱ የተባለ የማህበሩ አውራ የትግራይ ደም ቢኖረው ኖሮ ኢሳት ይህ ዓይኑ ያወጣ “የማህበረ ቅዱሳን” ወንጀል በዝምታ ያልፈው ነበር ወይ? እግዚኦ! እንደው ምላሳችሁ እስኪደማ: ሰሚ ጆሮም እስኪሰላች ድረስ “የማህበረ ቅዱሳን” ነገር ከአፋችሁ አይወጣም ነበር አይገልጸውም።
የመንግስት ባለ ስልጣን ስም ጠርታችሁ “አቶ እገሌ በጳጳሳት መካከል ተገኝተው እንዲህ ብለው ተናገሩ” በማለት አሉባልታ ከመዝራት ያልተመለሳችሁና ያላሳፈራችሁ ሰዎች እውነት ቢያንቃችሁ ምን ይደንቃል? የገዛ ራሳችሁ የፈጠራ ስራ “ተባለ: ተሰምቶል: የተገኘው ዜና ያብራራል” በሚል ፈሊጥ ያልተነገረና ያልተባለ የጽሑፉም ሆነ የድምጽ ማስረጃ በማታቀርቡበት: “ተባለ” ሲል ዜና ሰርቶ ያቀበላችሁ ሃላፊነት የሚወስድ ግለሰብም ሆነ የዜና ምንጭ በሌለበት “ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባቶች አቶ አባይ ጸሀዬ በግልጽ እንዳስታወቁት አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ማለት መንግስቱ ሀይለማሪያም ይመለስ ከማለት ተለይቶ አይታይም ማለታቸው ተሰምቶል። … አንዳንድ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ጳጳሳት በተለይም ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመለሱ ከሆነ እኛም አክሱም ላይ የራሳችን ሲኖዶስ እናቆቁማለን በማለት ቤተክርስቲያኒቱን በግልጽ በዘር መስመር ለማስቀመጥ ሀሳብ መሰንዘራቸውን የተገኘው ዜና ያብራራል።” ለማለት ግን የቀደማችሁ ማንም አልነበረም። (የኢሳት አማርኛ ዜና » ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ http://ethsat.com/2013/01/15/ቅዱስ-ሲኖዶስ-ያካሄደው-ስብሰባ-ውጥረት-የ/) እግዚኦ! ይብላኝ ይህን የፈጠራ ወሬአችሁ “እውነት ነው!” በማለት ከሰማይ እንደ ወረደ መና ሳያልምጥ ቃላችሁን አምኖ ለሚኖር ሕዝብ እንጅ በባለ አእምሮ ሰው ዘንድ እንካን ጨርሶ እንደማይሳካላችሁ ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail- yetdgnayalehe@gamil.com
United States of America


Leave a comment

አይቴ እረክቦ ለጋኔን ከመ እብሎ እንብየ ለጋኔን?

Read in PDF: Ayte Erekebo

መሪ ጥቅስ:

“በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል። ወይስ መጽሐፍ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን? ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። (7) እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።” ያዕቆብ 4፣ 1- 8

የጽሑፉ ዓላማ: ለሸቀጥ፣ የዋኁን ሕዝብ ለማታለልና ብሎም ለማደናገር ሲባል ብቻ በቆርጠህ ቀጥል ሥጋዊ መርህ እንዲሁም ፈሪሐ እግዚአብሔር በሌለበትና በማን አለብኝነት መንፈስ በድፍረት ተጀምሮ በቁንጽል የተተወ ቃለ-እግዚአብሔር ለመሙላት ተፃፈ። ከዚህ ያለፈ ጸሐፊው ሆኑ ጽሑፉ አንዱን በመደገፍ ሌላውን የማጥቃት ዓላማ የላቸውም። አሁንም ከታሰበበት ተዘግቶ የሚዘጋ በር የለምና ሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች ወደ ልባቸው ተመለሰው ከመከሩ ሰላም የማያወርዱበትና ዕርቅ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም ብለው ያምናሉ። ስድስተኛ ፓትሪያሪክ ለመምረጥና ለመሾም እየተጣደፈ የሚገኘው ሥርዓት አልባው የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ በተመለከተ በሚቀጥለው ጽሑፌ በስፋት የምንዳስሰው ይሆናል።

የጽሑፉ ውስኑነት: ጽሑፉ መቀመጫው ሰሜን አሜሪካ ያደረገ ጉባኤ የከሸፈውን “ዐርቀ ሰላም” ተከትሎ በያዝነው ወር 01/17/13 እ.አ.አ ለሰጠው መግለጫ ለማደናገሪያ እንደ መሪ ጥቅስ ሆኖ የተሰፈረውን አምላካዊ ቃል ዙሪያ ላይ የሚያትት ሥራ እንጅ ጽሑፉ ሙሉ የመግለጫውን ይዘት አይዳስስም።

Continue reading


Leave a comment

የዳንኤል ክብረት ክሽፈት

Read in PDF: Meksehefe ende Danel Kibret

ምንጭ፡-http://mesfinwoldemariam.wordpress.com

ጥር 2005

(አቶ ዳንኤል ክብረት በተለመደ ስሙ ዳንኤል ክስረት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን አዲስ መጽሐፍ አስመልክቶ በጻፈው መደዴ ጽኁፍ ያዘኑት ፕሮፌሰሩ የአላዋቂ ሳሚ ሌላ ነገር እንዳይለቀልቅ ብለው በብሎጋቸው ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ መልስ ሰጪ የለም ብሎ የድፍረት ጽኁፍን እያስነበበን የዘለቀውን አቶ ዳንኤል ከቤተክህነት ተንኮሉን እንጂ ሙያውን ስላልያዘ ፕሮፌሰሩ በትክክለኛ መጠሪያ ስሙ አቶ ዳንኤል ሲሉ ጠርተው ወዳጆቹ ባስቀመጡት ወንበር ላይ ሳይሆን በሚመጥነው ወንበር ላይ አስቀምጠውታል፡፡ ምላሹ ተገቢም ወቅታዊም አስፈላጊም በመሆኑ አንባቢያን እንዲያነቡት እንጋብዛለን፡፡ መልካም ንባብ)

አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር በ150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡

ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡

Continue reading


Leave a comment

ካህን ይመራሃል እንጂ አይከተልህም!

Read in pdf: Kahene

በዲ/ን ሙሉጌታ ወልድገብርኤል

የጽሑፉ ዓላማ:

ምንም አንኳን ለሺህ ዘመናት አብረው ቢኖሩና አሁንም አብረው ቢመላለሱ ዳሩ ግን በሚገባ ያልተዋወቁ

በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ምእመናንን አግብርተ እግዚአብሔር ከሆኑ እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህናት ጋር ለማስተዋወቅ ተጻፈ።

ማሳሰቢያ:

በዋናነት በጽሑፉ ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት ምእመናን እንደ አማኞችና ተከታዮች መጠበቅ የሚገባቸው ዋኖቻቸውን ይለዩና ክብር ለሚገባቸውም የሚገባቸውን ክብር ይሰጡ ዘንድ ተጻፈ እንጅ በክህነት ስም በቤተ ክርስትያን የመሸገውን ሰርጎ ገብ ወረበላ ሁላ እንዳሻው ይናጣችሁ የሚል መልዕክት የለውም:: ይህን ይሆን ዘንድም አልጻፍኩላችሁም።

በተጨማሪም ጽሑፉ በይዘቱ ኑሮ ለመሸወድ ተመሳስለው የተቀላቀሉ፣ ሁሉን በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት መንዳቢያንሳሉ በሰው ዘንድ እንደ መጋቢያን የሚታወቁና እንደ መጋቢም የሚጠሩ፣ “አባ/አቡነ እገሌ” ተብለው በሚጠሩ ጊዜም “አቤት” ለሚሉ መነኮሳት አይመለከትም። እውነተኛ ካህን ሲጠራ አቤት አይልም አይደለም አንድምታው ቁምነገሩ ያለው ወዲህ ነው። ያዕቆብ በስጋ ወላጅ አባቱ ከሆነው ከይህሳቅ ዘንድ እንዴት ምሩቃት እንደወሰደ እናውቃለን። ያዕቆብ ከአባቱ ምርቃት የወሰደበት መንገድ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሳይሆን ወንድሙን በመምሰልና በአባቱ ፊትም በቀረበ ጊዜም ያዕቆብ ሳለ ኤሳው ነኝ በማለት አባቱ በማታለል ነበር ምርቃቱን ሊያገኝ የተቻለው። ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ነበር እግዚአብሔርም ይባርከው ዘንድ “ስምህ ማነው?” ባለው ጊዜ በአባቱ ላይ ያደረጋትን የማታለል ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት አልሞከራትም። ለማስተላለፍ ተፈለገው መልዕክት ይሄ የሚያምነው የማያውቅ፣ ድግስ የማያመልጠው፣ እንደ ወርሀ መስከረም ዝንብ በዙሪያችን የሚያንጃብበውና ለሰውም “ለእግዚአብሔርም” ፈተና የሆነ ከማደሪያው ኮብልሎ ለከተመ “ፈላሲ” አይመለከትም ነው።

Continue reading


Leave a comment

ካህናቶቻችሁን አትበድሉ: ካህን ማለት የእድር ዕቃ ማለት አይደለምና!

Read in PDF: Kahenatocachehun

በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

መግቢያ:

የተራበ እንጅ የጠገበ ሰው ባያሳዝንም የሀገሬ ሰው “ከተራበ ይልቅ የጠገበ …” እንዲል ሰው ሲባል ሆዱ ሞልቶ/በልቶ ካደረ መጀመሪያ ጸብ የሚጀምረው ከፈጠሪው ጋር ለመሆኑ ስለሚበላና ስለሚጠጣ ጨርሶ ሃሳብ ለሌለው/የማይገባው ሰው ነገሩን ማውሳት በራሱ ቀባሪን የማርዳት ያክል ነው የሚሆነው። አንድ ሰው ስለሚላው፣ ስለሚጠጣውና ስለሚያርፍበት መጠሊያ ስፍራም የሚያሳስበው ነገር ከሌለ ባለቤት ከሌለው ከሜዳ አህያ የሚለየው በተፈጥሮ ብቻ ይሆናል። አንድ እውነት አለ ይኸውም: አንድ ከድህነት ወለል በታች ይኖር የነበረ ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀድሞ በነበረው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ይኖር ሳለ ያላየውን ሀብትና ንብረት ማፍራት ሲጀምር የቀድሞ ህይወቱን የዘነጋ እንደሆነ በቀላሉ የነበረውን ታላቅህን የማክበር ባህሪ፣ በሰዎች መካከል የነበረውን ፍቅርንና ይታይበት የነበረውን ትህትና በአጠቃላይ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አጥቶ ሣር ቅጠሉ ሁላ “ምን አልክ አንተ? …” እያለ ግዑዙን አካል ሳይቀር እያገላመጠ ከራሱ ጥላ እስከመጣላት ድረስ መሄዱ የማይቀር ነው።

ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ዘንዳ በዛሬው ዕለት ላካፍላችሁ ወደ ወደድኩት ወደ ቅድመ ፍሬ ነገሬ/መልዕክት ሳልፍ ለጽሑፌ መነሻ የሆነኝን ነጥብ እንደሚከተለው በአጭሩ ላስቀምጥ። በዕረፍት እንዲሁም በአንዳንድ ጉዳዮች ምክንያት በአሜሪካ ጥቂት የማይባሉ ክፍለ ግዛቶች ለመዘዋወር ዕድሉ ገጥሞኝ በማደርጋቸው ጉብኝቶች ሁሉ በሄድኩበት ክፍለ ግዛት እናት ቤተ ክርስቲያኔን ጎራ ሳልል የተመለስኩበት ዕለት የለም። በጉብኝቴ ወቅትም በርካታ መጠሪያ ያላቸው አብያተ ክርስትያናት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት አገልጋዮችና ደቀ መዛሙርት እንዲሁም የምእመናን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ችያለሁ። ታድያ በእነዚህ ሁሉ ቀናት ለመታዘብ እንደቻልኩ በሀገር ቤት የምትገኘውን “ቤተ ክርስትያን” የራሱ መልክና ገጽታ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተዘፍቃ እንደምትገኝ ሁሉ በውጭው ዓለም በተለይ በሰሜን አሜሪካ የምትገኘው “ጉባኤም” እንዲሁ ራሱ በቻለ ሌላ ገጽታ ያለው በቀላሉ የማይታለፍና ምናልባትም አሉ በማለት ልንዘረዝራቸው የምንችላቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮች ሁሉ እንደ ምንጭ ሊወሰድ የሚችል ትርጉሙ የጠፋበት “የቤተ ክርስቲያን” ምስረታ፣ በአገልጋዮች ካህናትና በምእመናን መካከል ያለውን መራራ ግኑኝነት፤ እንደው ካህን እንደ ምጻተኛ፣ የእድር ዕቃ ያክልም ክብር የሌለውና በአንጻሩ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያላቸው ባለሀብቶች በገንዘባቸው ብዛት፣ በቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቀድሞ መጠሪያቸውና ማዕረጋቸው፣ በአስኳላው ሚዛን የሚደፉ ግለሰቦችም እንዲሁ ነን/አለን በሚሉት ሁሉ ፍጥጥ ባለ መልኩ እንደፈለጉ የሚሆኑበትን አሳዛኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁኔታ አንስተን በአጭሩ እንወያያለን።

Continue reading


Leave a comment

ቤተክርስቲያንና የገባችበት አጣብቂኝ

REd in PDF

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በታሪክዋ የተለያየ ፈተናዎች ገጥመዋት የሚያውቁ ቢሆንም እንደ አሁኑ አይነት ግን የተለየ መልክ ያለው አደጋ ገጥሟት አያውቅም። የቤተክርስቲያን አባቶች ቤተክርስቲያኒቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ መውሰድ የሚገባቸው ጥበብ የተሞላበት እርምጃን ሲወስዱ እየታዩ አይደለም። በዙሪያዋ ተሰብስበው የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ያሉ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ማኅበራትም ችግሩ የሚጋጋልበትን መንገድ በመፈልግ ነገሮችን ከማራገብ በተሻለ እያደረጉት የሚገኝ ገምቢ እንቅስቃሴ የለም።

የሁለቱም ሲኖዶስ አባላት ከአንዳንድ አስተዋይ አባቶች በስተቀር ለእርቁ ተገቢውን ትኩረት እየሰጡ አይደለም። የዜና ማሰራጫዎችም “ጎሽ እንኳን አልተስማማችሁ” ከሚል የዘለለ ገምቢ ሚና ሲጫወቱ አይታዩም። በሁሉም ነገር የራሱን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ከመሯሯጥ የዘለለ በእውነት ለቤተክርስያኒቱ አንድነት በቅንነት ተገቢ ሚና የሚጫወት አለ ለማለት በማያስደፍር ሁኔታ ነገሮች ሲጦዙ እየተመለከትን ነው። በአዲስ አበባው ሲኖዶስ በኩል ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ይልቅ የቁጥር ስሌት አንገብጋቢ ሁኖ ይታያል። በአሜሪካው ሲኖዶስ በኩልም ወደ እርቅ የማያደርሱ እርምጃዎች በአንዳንድ ጳጳሳት አማካኝነት እየተወሰደ ይገኛል። በቅርቡ ኤርትራ ሄደው የመንግስትን ተቃዋሚዎች ባርከው የተመለሱት ጳጳስ እንቅስቃሴም ይብዛም ይነስም በእርቁ ላይ ጠባሳ ማሳደሩ አይቀርም። በዚህኛው ሲኖዶስ በኩልም እርቅ እየተወራ በምርጫ ጉዳይ ጊዜ ማጥፋቱ በእርቁ ላይ የተደቀነ ስጋት ነው።

እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ ማኅበርም በተገኙ አጋጣሚዎች የራስን ፋላጎት ለማስፈጸም ከመድከም በተለየ በእውነት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲፈጠር ፍላጎት ያለው አይደለም። የውጪውን ሲኖዶስ ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ ቀድሞ ያወገዘው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በአስራ ዘጠኝ ዘጠናዎቹ ውስጥ በሚታተም ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ የአሜሪካውን ሲኖዶስ ደጋግሞ ማውገዙ የሚታወስ ነው። ማኅበሩ በአሜሪካው ሲኖዶስ ላይ የጣለውን ወፈ ግዝት ማንሳቱን በተመለከተም በይፋ የነገረን ነገር የለም

Continue reading


Leave a comment

ራሱን እንደ ግብጹ ሙስሊም ብራዘርሁድ የሚቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን የብጥብጥ አዋጅ አወጀ

Read in PDF: muslim Brotherhood

ምርጫውን በተመለከተ የነገሮች አካሄድ እንደፈለገው ያልሆነለት ማኅበረ ቅዱሳን ተስፋ የቆረጠ በሚመስል ስሜት ህዝቡ ይፋ ተቃውሞ እንዲያሰማ ጠየቀ፡፡ በአንድ አድርገን ብሎጉ በኩል የ”ግልጽ የአካል ተቃውሞ” ጥሪ ያቀረበው ማህበሩ አባላቱ ብላቴ ላይ የሰለጠኑበት ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን ፍንጭ የሚሰጥ ጥሪ ነው ተብሎለታል፡፡ “በተግባር ተቃውሞዋችንን እንግለጽ” በሚል ርዕስ የወጣው ጽኁፍ አላማው የማኅበሩን ኦሪታዊ ደጋፊዎች አዲሱን ኪዳን በማያውቀው ማንነታቸው ለአመጽ እና ለብጥብጥ ማነሳሳት መሆኑ ታውቋል፡፡

አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ እንደማይፈልጉ እና ይልቁንም እርቁን እሳቸው መጥተው በማረፊያ ቤት በሚቆዩበት አሰራር ብቻ እንደፈታ እንደሚፈልጉ በአሜሪካ ሬዲዩ ላይ በዘወርዋራ መንገድ የገለጡት የማኅበሩ ዋና ሰዎች እና የሴት ነገር የማይሆንላቸው ዳንኤል ክስረት እና አባይነህ ዋሼ ማኅበሩ የአዲስ አበባውን ሲኖዶስ ተቆጣጥሮ የሚፈልገውን ነገር የማድረግ ህልሞ እንደሚፈጸም ቢያምኑም ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡፡ ፡

Continue reading

Follow

Get every new post delivered to your Inbox.

Join 209 other followers