አውደ ምሕረት

ቅዱስ ሲኖዶሱና ዘጠነኛ ቀኑ

6 Comments

  • አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ላለማስረከብ አስቂኝ መከራከሪያ አቀረቡ
  • ማኅበሯ ሌላው መንገድ ሁሉ አላስኬድ ሲላት አይመጥንም በሚል የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊነትን ከመምኅር እንቁባህሪ ላይ ለመንጠቅ የምታድረገው ሙከራ አልተሳካላትም።
  • ማኅበረ ቅዱሳንንየመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ውድቅ እንዲሆን እንቅልፍ አጥቶበት የነበረ ሲሆን እንደገና እንዲጠና ታዟል።   
አባ አብርሃም ርስት ጉልቴ ነው ያሉትን የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ የታዘዙትን ትዕዛዝ ለመቃመም ከተነሳው ጥያቄ ጋር የማይሄድ እኔ ከእርስዎ እሻላለሁ የሚል መከራከሪያ አቀረቡ። እኔ ምን አለኝ እና ነው መልስ የምባለው ሲሉ የነበሩት ሰው አሁን በራሴ ወጪ አጣሪ ተልኮ ከእኔ እና ከእርሰዎ ማን ጥሩ ስራ እንደሰራ ይጣራ? ሲሉ ጠይቀዋል። ይህም ጥያቄ አሜሪካ ለመመለስ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት ያሳያል ተብሏል። ስውየውን የሚያስጨንቃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተገኝተው አባትነትን ማሳየት ሳይሆን ጥቅምና ምቾት ባለበት ቦታ ላይ መንቀባረር መሆኑንም አሜሪካ ለመመለስ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ያሳያል።
አሁን በቅርቡ እንኳ ወደ ሐረር ሀገረ ስብከት እንደ ደረሱ ለኔ የተመደበችው መኪና የትኛዋ ነች ብለው ሲጠይቁከእሳቸው በፊት ነበሩት አቡነ ዮሴፍ ይሄዱበት የነበረቸውን መኪና ሲያሳዩዋቸው ከት በለው ስቀው እኔ በዚህ መኪና ልሄድ? ብለው ጠይቀው ይህ መኪና ስለማይመጥነኝ በአስቸኳይ ከሞኤንኮ አዲስ መኪና ይገዛ ብለው አዲስ መኪና አስገዝተው በእስዋ መንፈላሰፍ ጀምረዋል። ድንቄም አባትነት።

የእሳቸው አቸፍቻፊ የሆነውና አሁን የማህበረ ቅዱሳን መሆኑን በበቂ ማስረጃ ዲ/ን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል ያረጋገጠው ደጀ ሰላም ብሎግ አጣሪ ይላክ ስላሉ “ብፁዕ አቡነ አብርሃም አቡነ ፋኑኤልን ተቋቋሙ” - ሲል ለፍፏል። መቋቋም በምን? እኔ የተሻለ ሥራ ሠርቻለሁ በማለት ለራስ ምስክርነት በመስጠት ወይስ? በእርግጥ ሥራ በመስራት? አቸፍቻፊዋ ደጀ ሰላም ለማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ነጻ የመሰብሰቢያና ሴራ የመሸረቢያ ቦታ የሆነውን የሃገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ላለመመለስ ምን በቂ ምክንያት አለ? ለሚለው ምንም ምላሽ ሳትሰጥ ሕገ ወጡንና ሀፍረተ ቢሱን አባት አባ አብርሃምን አይኗን ጨፍና መደገፏን አቁማ በሚመስል ምክንያት እንኳ እንድትደግፍ እንመክራታለን።
ለነገሩ ለማቅ የሚያስጨንቀው የማሕበሩ ሕለውና ነው እንጂ የቤተክርስቲያን ህልውና ስላልሆነ ለማህበሩ አይናቸውን ጨፍነው ለሚታዘዙት አባት አይኑን ጨፍኖ መከራከሩ አይገርምም።
የሰንበት ማደራጃውን ጉዳይ አሁንም በተለያየ ዘዴ ለማሳካት እየሞኮረ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ደግሞ መምህር እንቆባሕሪይ ለቦታው አይመጥኑም የሚል መከራከሪያ አቅርቦዋል። የተመሰከረላቸው የአቋቋም መምህር የሆኑትን በማደራጃ መምሪያው በምክትል ኃላፊነት ከ10 አመት በላይ የሰሩት መምህር ዕንቆባህሪ ለቦታው አይመጥኑም ብሎ ማሰብም መከራከሪያ ማቅረብም አሳፋሪ ነገር ነው። ለዛውም ደግሞ
ከአንድ ደብር አቃቢነት የዘለለ ስልጣን ባልነበራቸውና በማደራጀው ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳንን ፍላጎት በማስፈጸም ለ6 ወራት ቆይተው የነበሩት አባ ኅሩይ ከመምህሩ የተሻሉ ናቸው ብሎ ማውራቱ የሁለቱንም ሰዎች ሥራና ኃላፊነት ለሚያውቁ ሰዎች የሚያሳዝን ነው። ማቅ መምህሩ አይመጥኑም የሚል መከራከሪያ ያነሳው መምህሩ ስለማይመጥኑ ሳይሆን ለኔ አይታዘዙም ከሚል መነሻ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳንን የመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ ጥናቱ በቀረበ ጊዜ ቅዱሳን አባቶች በትጥናቱ ሙሉ በሙሉ ተስማምተው የነበሩ ቢሆንም ማቅ ልፈርስ እችላለሁ በማለት ደጋፊ ጳጳሳትዋን ቀስቅሳ እንደገና ይጠና ወደሚል ውሳኔ ተወስኗል።  የማኅበሯ ፍላጎት ውድቅ እንዲሆን ቢሆንም እንደገና ይጠና መባሉ ታውቋል።
እርቀ ሰላሙን በተመለከተ የማቅ ብሎጎች አቡነ ጳውሎስን ለማጥላላት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እሳቸው ግን እርቀ ሰላሙን እንደሚፈልጉትና መካሔዱም ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። እሳቸውን ለማጥላላት የሚሞክሩበት ዋነኛው ምክንያትም የአሜሪካው ሲኖዶስ የእነሱን ዘገባ አምኖ በእርቁ ላይ ልቡን እንዲደፍን ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የእርቀ ሰላሙ መሳካት ለህልውናዬ አደጋ ነው ብሎ ያምናል። እርቀ ሰለሙ በሐምሌ ወር ይቀጥላል።
                               
About these ads

Author: Awde Mihret

it is eotc blog

6 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶሱና ዘጠነኛ ቀኑ

  1. Awde Mihiret Bertu Melkam neger takerbalachihu Mr Enkobahiry Mulu sew New -yetemare sew New-Menfesawinm ZemenawiwnimCiyagelegil yenore sew new -mahiletaw-dimtsawi- Abba Hiruy Moya Yele-Melk Yele -Hiywot yele-Kumet yele -(ciyayut yalamare sibelut yimeral)Addis Abeba Pawilos Gebto Menafik Hono Bemegegetu Sayimar yetebarere-Naziret wilncet Serko Yetebarere -Amerka Gebito Bositen Benewr yeteyaze-Kansas Sewn siyadebabib yenore -Tax Ciyasadidi Genzebi sisebesib yenore-Kidane Mihiret Church yetekarayeletn Menoriya bet lesew akerayito yatalele -Sanhoze st Gebreil Hedo Genzebuin wesido yetefa Delala new Abba Hiruy Abune Markosina Abune Abirham Gojam Bemehonu Abune Pawlosin leminew yashomut zerega sew new Leminm ayimetinim Mastemar ayichil Mekedes ayichil yasazina Mahibere Kidusan sile Aba Hiruy Hulunim Neger yawkal Betsam Yaferkut mahibere kidusan Aba Hiruyin Degifo Mr Enkobahiryin Mekawem sijemir new

  2. uhhhhhhhhhhhhhhhh techet becha. betekeristianin wegeno tenagari tefa. hod amlaku hula!!!!!!!!!!

  3. Ewunet eyader yewetal enj ayedbekem, mahiber kidusan yemot gudiguad lerasu eyekofer newu. Ye hama sera berasu lay ketatun eyesete newu, bertu amelakachen kenanit gar yehun,

  4. ማህበረ ቅዱሳን ዛሬም የማይተኛ ክፉ መንፈስ ነው ፣ እግዚአብሔር ግን ሁል ዘገዜ አሸናፊ ነው። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋልና እናንተም ዝም ትላላችሁ ዘፀዓት ም 14 ቁጥር 14። ዐውደ ምህረቶች አሁን በርቱ እዉነቱን ከማውጣት ዝም አበሉ። ማቅ ዛሬ እራቁቱ ዝለ ቀረ ደስ ይባላችሁ………..

  5. awdemhret endih ewnetun eyawetachu yihn tikimegna mahber agalitu betekrihstian lemafres yetezegaju silehonu yemaikofrut dingay yelem .

  6. Dejeselam gud felabet Mahiber kidusan ye hama yet sekelebet meskeya lerasu eyazegaj newu.Ye Orthodox hezebu mahiberun tefawu semunim mesmat telawu. Egizeabeher yemesegen lehulum ……….

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

Follow

Get every new post delivered to your Inbox.

Join 209 other followers